የጥበብ መንገዶች
1የጥበብ ሁሉ መገኛዋ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፥ ለዘለዓለምም ከእርሱ ጋር ናት። 2የባሕር አሸዋን፥ የዝናም ጠብታን፥ የዘለዓለምነት ቀኖችንስ ማን ቈጠረ? 3የሰማይን ምጥቀት፥ የምድርን ስፋት፥ የባሕርን ጥልቀት፥ ጥበብንም ማን መርምሮ አገኛቸው? 4ጥበብ ከሁሉ አስቀድሞ ተፈጠረች። 5የጥበብ መታሰቧ ከጥንት ጀምሮ ነው። 6የጥበብ ሥርዋ ለማን ተገለጠ? 7ምክሯንስ ማን ዐወቀ? 8ጥበበኛ አንድ ነው፥ እጅግም የሚያስፈራ ነው፤ 9እርሱ እግዚአብሔር ሠራት፤ አያት፥ ሰፈራትም። 10እርስዋም እንደ እርሱ ስጦታ ከሥጋዊ ሁሉ ጋር ናት፥ 11እግዚአብሔርን መፍራት ክብር ነው፥ 12እግዚአብሔርን መፍራት የልብ ደስታ ነው፤ 13እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ፍጻሜው ያምራል፤ 14የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ 15ከሰዎችም ጋር የዓለምን መሠረት ፈጠረች፤ 16ጥበብን መጥገብ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥ 17በቤቶችዋም ደስታ መልትዋል፥ 18የጥበብ ዘውድዋ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ 19ፈጣሪዋ አያት፥ ሰፈራትም፥ 20የጥበብ ሥር እግዚአብሔርን መፍራት ነው፥