የዮዲት የምስጋና መዝሙር
1ዮዲትም ይህቺን የምስጋና መዝሙር በእስራኤል ሁሉ ዘንድ ትዘምር ጀመረች፤ ሕዝቡም ሁሉ ይህቺን የምስጋና መዝሙር ከእርስዋ ቀጥለው ዘመሩ። 2ዮዲትም አለች፥ “አምላኬን በከበሮ አመስግኑት፤ 3እግዚአብሔር በጦርነት ጦርን ያሸንፋልና። 4ስሙም እግዚአብሔር ነው፤ 5አሦራውያን በመስዕ በኩል ከተራራው ወጡ፤ 6አውራጃችንን በእሳት ያቃጥሉ ዘንድ፥ 7ነገር ግን ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር በሴት እጅ አጠፋቸው። 8አርበኛቸው በጐልማሳ እጅ ድል አልተነሣምና፥ 9የመበለትነቷንም ልብስ በእስራኤል ዘንድ ስለሚጨነቁት ሰዎች ስትል ተወች። 10ፊትዋንም ሽቱ ተቀባች፤ 11ጫማዎችዋም ዐይኖቹን በዘበዙ፤ 12ከመደፋፈርዋም የተነሣ የፋርስ ሰዎች ደነገጡ፤ 13ያንጊዜ የተጨነቁ ወገኖች ደስ ብሏቸው ደነፉ፤ 14የሴቶች ልጆች ልጆችም አሳድደው ወጓቸው፤ 15ለእግዚአብሔር መዝሙር እዘምራለሁ፤ 16እግዚአብሔር ሆይ፥ ገናና ነህ፤ 17ፍጥረትህ ሁሉ ለአንተ ይገዛሉ፤ 18ተራሮች ከውኆች ጋር ከመሠረቶቻቸው ይነዋወጣሉና፤ 19መሥዋዕቱ ሁሉ ለበጎ መዓዛ አይበቃምና፥ 20በወገኖች ላይ በጠላትነት ለሚነሡ ለአሕዛብ ወዮላቸው፤ 21በሥጋቸውም እሳትና ትልን ይልክባቸዋል፤ 22ወደ ኢየሩሳሌምም በደረሱ ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰገዱ፤ ሕዝቡም ራሳቸውን ባነጹ ጊዜ የሚቃጠለውን መሥዋዕታቸውንና የፈቃድ ቍርባናቸውን፥ ስጦታቸውንም አቀረቡ። 23ዮዲትም ሕዝቡ የሰጧትን የሆሎፎርኒስን ገንዘብ፥ ከመኝታ ቤቱም የወሰደችውን የራስጌውን ሰይፍ ለመታሰቢያ ለእግዚአብሔር ሰጠች። 24ሕዝቡም በኢየሩሳሌም በቤተ መቅደስ ፊት ሦስት ወር ደስታ አደረጉ፤ ዮዲትም ከእነርሱ ጋር ተቀመጠች። 25ከእነዚያም ወራት በኋላ ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ ተመለሰ፤ ዮዲትም ወደ ቤጤልዋ ተመልሳ በንብረቷ ኖረች፤ በዘመኗም በሀገሩ ሁሉ የከበረች ሆነች። 26የሚፈልጓትም ብዙዎች ነበሩ፤ ባሏ ምናሴ ሞቶ በወገኖቹ ዘንድ ከተቀበረ ጀምሮ በሕይወት ዘመኗ ሁሉ በግብር ያወቃት ሰው የለም። 27ፈጽማም በክብር ገነነች። 28በባሏ በምናሴም ቤት እስክታረጅ ድረስ ኖረች፤ ዕድሜዋም መቶ ዐምስት ዐመት ነበር፤ ያችንም ብላቴናዋን ነጻ አወጣቻት፤ በቤጤልዋ ሞታ በባሏ በምናሴ ዋሻ ተቀበረች፤ 29የእስራኤልም ወገኖች ሰባት ቀን አለቀሱላት፤ ከመሞትዋም በፊት ገንዘብዋን ለባልዋ ለምናሴ አቅራቢያና ለእርሷ አቅራቢያ ለሆኑ ዘመዶችዋ አካፈለች። 30የእስራኤልንም ልጆች በዮዲት ዘመን፥ ዳግመኛም እርስዋ ከሞተች በኋላ ለብዙ ዘመን ያስፈራቸው አልነበረም።