የዳዊት መዝሙር ከጠላቶቹ በዳነ ጊዜ
1ዳዊትም እግዚአብሔር ከሳኦል እጅና ከጠላቶቹ ሁሉ እጅ ባዳነው ቀን የዚህን መዝሙር ቃል ለእግዚአብሔር ተናገረ። 2እንዲህም አለ፥ “እግዚአብሔር ዓለቴ፥ አምባዬም፥ መድኀኒቴም ነው፤ 3እግዚአብሔር ጠባቂዬ ነው፤ በእርሱም እታመናለሁ፤ 4ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፤ 5የሞት ጭንቅ ያዘኝ፤ 6የሞት ጣር ከበበኝ፤ 7በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፤ 8ምድርም ተንቀጠቀጠች፤ ተናወጠችም፤ 9ከቍጣው ጢስ ወጣ፤ 10ሰማዮችን አዘነበለ፤ ወረደም፤ 11በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፤ 12መሰወርያውን ጨለማ አደረገ፤ 13በፊቱም ካለው ብርሃን የተነሣ ፍም ተቃጠለ። 14እግዚአብሔርም ከሰማይ አንጐደጐደ፤ 15ፍላጻውን ላከ፤ በተናቸውም፤ 16ከእግዚአብሔር ተግሣፅ የተነሣ፥ 17ከላይ ላከ፤ ወሰደኝም፤ 18ከብርቱዎች ጠላቶቼ፥ 19በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፤ 20ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ 21እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ 22የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ 23ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበርና፤ 24በእርሱ ዘንድ ንጹሕ እሆናለሁ፤ 25እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ፥ 26ከጻድቅ ጋር ጻድቅ ትሆናለህ፤ 27ከተመረጠም ጋር የተመረጠ ትሆናለህ፤ 28አንተ የተዋረደውን ሕዝብ ታድናለህና፤ 29አቤቱ! አንተ መብራቴ ነህና፤ 30በአንተ ብቻዬን እሮጣለሁና፤ 31የኀያል አምላክ መንገድ ንጹሕ ነው፤ 32ከእግዚአብሔር በቀር ጽኑዕ ማን ነው? 33በኀይል የሚያጸናኝ ኀያል እርሱ ነው፤ 34እግሮቼን እንደ ዋልያ እግሮች አጸና፤ 35ለእጆቼ ጦርነትን ያስተምራል፤ 36የመድኀኒቴንም ጋሻ ሰጠኸኝ፤ 37በሜዳም አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፤ 38ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ፤ አጠፋቸውማለሁ፤ 39እቀጠቅጣቸዋለሁ፤ መቆምም አይችሉም፤ 40በጦርነትም ጊዜ በኀይል ታጸናኛለህ፤ 41የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፤ 42ጮኹ፤ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ 43በነፋስ ፊት እንዳለ እንደ ምድር ትቢያ ፈጨኋቸው፤ 44ከአሕዛብ ጠብ አድነኝ፤ 45የባዕድ ልጆች ዋሹኝ፤ 46የባዕድ ልጆች አረጁ፤ 47እግዚአብሔር ሕያው ነው፤ ጠባቂዬም ቡሩክ ነው፤ 48በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ ጽኑዕ ነው። 49ከጠላቶቼ የሚያወጣኝ እርሱ ነው፤ 50አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ 51የንጉሡን መድኀኒት ታላቅ ያደርጋል፤