የማቴዎስ ወንጌል 4
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መፈተን
1ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው። 2አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ። 3ፈታኝም ቀርቦ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል!” አለው። 4እርሱም መልሶ “ ‘ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፎአል” አለው። 5ከዚህ በኋላ ዲያቢሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ 6“ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤
ጌታችን የማስተማር ሥራውን እንደጀመረ
12ኢየሱስም ዮሐንስ አልፎ እንደ ተሰጠ በሰማ ጊዜ ወደ ገሊላ ፈቀቅ ብሎ ሄደ። 13ናዝሬትንም ትቶ በዛብሎንና በንፍታሌም አገር በባሕር አጠገብ ወደ አለችው ወደ ቅፍርናሆም መጥቶ ኖረ። 14በነቢዩም በኢሳይያስ እንዲህ የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ፤ 15ምድርና የንፍታሌም ምድር፥ 16ቀመጠው ሕዝብ ታላቅ ብርሃን አየ፤
አራቱ ዓሣ አጥማጆች እንደተጠሩ
18በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና። 19እርሱም “በኋላዬ ኑ፤ ሰዎችንም አጥማጆች እንድትሆኑ አደርጋችኋለሁ” አላቸው። 20ወዲያውም መረባቸውን ትተው ተከተሉት። 21ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም። 22እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት።
ኢየሱስ ብዙ ሰዎችን እንደፈወሰ
23ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር። 24ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም። 25ከገሊላም ከዐሥሩ ከተማም ከኢየሩሳሌምም ከይሁዳም ከዮርዳኖስም ማዶ ብዙ ሕዝብ ተከተሉት።