የኢየሩሳሌም መከራና ኀዘን
1አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! 2ቤት። በሌሊት እጅግ ታለቅሳለች፤ 3ጋሜል። ይሁዳ ስለ ውርደቷና ስለ ባርነቷ ብዛት ተሰደደች፤ 4ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፤ 5ሄ። ስለ ኀጢአቷ ብዛት እግዚአብሔር አዋርዶአታልና 6ዋው። ከጽዮን ሴት ልጅ ውበት ሁሉ ተወስዶአል፤ 7ዛይ። ኢየሩሳሌም ቀድሞ ወድዳ በሠራችው ሥራ ሁሉ የመከራዋን ወራት አሰበች፤ 8ሔት። ኢየሩሳሌም እጅግ ኀጢአት ሠርታለች፤ ስለዚህ ረክሳለች፤ 9ጤት። ግዳጅዋ ከእግርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻሜዋን አላሰበችም፤ 10ዮድ። አስጨናቂው በምኞቷ ሁሉ ላይ እጁን ዘረጋ፤ 11ካፍ። ሕዝብዋ ሁሉ እንጀራ አጥተው ያለቅሳሉ፤ 12ላሜድ። እናንተ መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ! በእናንተ ዘንድ ምንም የለምን? 13ሜም። ከላይ እሳትን ሰደደ፤ አጥንቶችንም አቃጠለ፤ 14ኖን። በእጄ ስለተታቱ ኀጢአቶች ተጋ፤ 15ሳምኬት። እግዚአብሔር ኀያላኖችን ሁሉ ከመካከሌ አስወገዳቸው፤ 16ዔ። የሚያጽናናኝ፥ ነፍሴንም የሚመልሳት ከእኔ ርቆአልና ዐይኔ ውኃ ያፈስሳል። 17ፌ። ጽዮን እጅዋን ዘረጋች፤ የሚያጽናናትም የለም፤ 18ጻዴ። ቃሉን አማርሬአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። 19ቆፍ። ወዳጆችን ጠራሁ፤ እነርሱም ቸል አሉኝ፤ 20ሬስ። አቤቱ! ተጨንቄአለሁና፥ አንጀቴም ታውኮብኛልና ተመልከት፤ 21ሣን። እኔ እንደማለቅስ ሰምተዋል፤ የሚያጽናናኝ የለም፤ 22ታው። ልቅሶዬ እጅግ ነውና፥ ልቤም ደክሞአልና፥