ጸሎተ ዮናስ
1እግዚአብሔርም ዮናስን ይውጠው ዘንድ ታላቅ ዓሣ አንበሪን አዘዘ፤ ዮናስም ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣ አንበሪው ሆድ ውስጥ ነበረ። 2ዮናስም በዓሣ አንበሪው ሆድ ውስጥ ሆኖ ወደ አምላኩ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፥ 3“በመከራዬ ሳለሁ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፤ 4ወደ ጥልቁ ወደ ባሕሩ ውስጥ ጣልኸኝ፥ 5እኔም፦ ከዐይንህ ፊት ተጣልሁ፤ 6ውኃ እስከ ነፍሴ ድረስ ፈሰሰ፤ 7እነሆ ራሴ ወደ ታች ወደ ተራሮች መሠረት ወረደ፤ 8ነፍሴ በዛለችብኝ ጊዜ እግዚአብሔርን አሰብሁት፤ 9ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ፤ 10እኔ ግን ከምስጋናና ከኑዛዜ ቃል ጋር እሠዋልሃለሁ፤ 11እግዚአብሔርም ዓሣ አንበሪውን አዘዘው፤ እርሱም ዮናስን በየብስ ላይ ተፋው።