መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 16
1የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፤ ዳዊትም በተከለላት ድንኳን ውስጥ አኖሩአት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕትም በእግዚአብሔር ፊት አቀረቡ። 2ዳዊትም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የደኅንነቱን መሥዋዕት ማቅረብ በፈጸመ ጊዜ በእግዚአብሔር ስም ሕዝቡን ባረከ። 3ለእስራኤልም ለወንዱም ለሴቱም ለእያንዳንዱ አንዳንድ እንጀራ፥ አንዳንድም ቍራጭ ሥጋ፥ አንዳንድም የዘቢብ ጥፍጥፍ አካፈለ። 4በእግዚአብሔርም ታቦት ፊት ያገለግሉ ዘንድ፥ የእስራኤልንም አምላክ እግዚአብሔርን ያወድሱት ዘንድ፥ ያመሰግኑትና ያከብሩትም ዘንድ ከሌዋውያን ወገን አቆመ። 5አለቃውም አሳፍ ነበረ፤ ከእርሱም ቀጥሎ ዘካርያስ፥ ኢያሔል፥ ሰሜራሞት፥ ይሔኤል፥ ማታትያ፥ ኤልያብ፥ በናያስ፥ አብዲዶም፥ ይዒኤል በመሰንቆና በበገና፥ አሳፍም በጸናጽል ይዘምሩ ነበር። 6ካህናቱም በናያስና የሕዜኤል በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት ፊት ሁልጊዜ መለከት ይነፉ ነበር። 7በዚያም ቀን ዳዊት በአሳፍና በወንድሞቹ እጅ እግዝአብሔርን እንዲያመሰግኑ አስቀድሞ ትእዛዝን ሰጠ።
የምስጋና መዝሙር
8የእስራኤል ልጆች በእግዚአብሔር ታቦት ፊት የዘመርዋት መዝሙር ይህች ናት፦ 9ለእግዚአብሔር ተቀኙለት፥ ዘምሩለት፤ 10በቅዱስ ስሙ ክበሩ፤ 11እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ 12የሠራትን ድንቅ አስቡ፥ 13ባሪያዎቹ የእስራኤል ዘር፥ 14እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ 15ቃል ኪዳኑን ለዘለዓለም፥ 16ለአብርሃም ያደረገውን፥ 17ለያዕቆብ ሥርዐት እንዲሆን 18እንዲህም አለ፥ “ለአንተ የከነዓንን ምድር 19ይህም የሆነው እነርሱ በቍጥር ጥቂቶች ሰዎች፥ 20ከሕዝብ ወደ ሕዝብ፥ 21ሰው ግፍ ያደርግባቸው ዘንድ አልፈቀደም፤ 22“የቀባኋቸውን አትንኩ፥ 23ምድር ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ 24ክብሩን ለአሕዛብ፥ 25እግዚአብሔር ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፤ 26የአሕዛብ አማልክት ሁሉ ጣዖታት ናቸው፤ 27ክብርና ግርማ በፊቱ፥ 28እናንተ የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሔር አምጡ፥ 29ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ 30ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጣለች፤ 31ሰማያት ደስ ይበላቸው፥ ምድርም ሐሤትን ታድርግ፤ 32ባሕር በሞላዋ ትናወጣለች፤ 33በምድር ሊፈርድ ይመጣልና፥ 34እግዚአብሔርን አመስግኑ። 35የመዳናችን አምላክ ሆይ፥ አድነን፤ 36ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም፥
ሥርዐተ አምልኮ
37እንዲሁም በየቀኑ እንደሚገባቸው በታቦቱ ፊት ዘወትር ያገለግሉ ዘንድ አሳፍንና ወንድሞቹን ተዋቸው። 38አብዲዶምንም፥ ስድሳ ስምንቱንም ወንድሞቻቸውን፤ የኤዶታምም ልጅ አብዲዶምና ሖሳ በረኞች ይሆኑ ዘንድ ተዋቸው፤ 39ካህኑን ሳዶቅንና ካህናቱን ወንድሞቹን በገባዖን በኮረብታው መስገጃ ባለው በእግዚአብሔር ማደሪያ ፊት አቆማቸው፥ 40ለእስራኤልም ልጆች ይነግራቸው ዘንድ አገልጋዩ ሙሴን እንደ አዘዘው በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁልጊዜ ጥዋትና ማታ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ። 41ምሕረቱም ለዘለዓለም ነውና እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ዘንድ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸው የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር አቆመ። 42ከእነርሱም ጋር ካህናቱ ከፍ አድርገው ለማሰማት መለከትና ጸናጽል ለእግዚአብሔርም መዝሙራት የዜማ ዕቃ ይዘው ነበር፤ የኤዶታም ልጆች ግን በረኞች ነበሩ። 43ሕዝቡ ሁሉ እያንዳንዱ ወደ ቤቱ ሄደ፤ ዳዊትም ቤቱን ይባርክ ዘንድ ተመለሰ።